Skip to main content

Jerusalem Spiritual Tour

Ghion Travel offers a carefully planned Tour package that enables you to visit the sacred sites of Jerusalem, Nazareth, Bethlehem, and much more at ease.

“ኢየሩሳሌምሆይእግሮቻችንበአደባባይሽቆሙ”
ይህንየታሪክአጋጣሚይጠቀሙበት:-

ለረጅም ጊዜ ሲመኙት የነበረውን ምኞት ቅድስት አገር ኢየሩሳሌምን በመጎብኘት ይፈጽሙት።
ለዚህም “ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ” የሚለው ቃል መንፈሳዊ ጥሪያችን ነው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጸነሰባትን፣ የተወለደባትን፣ ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራት የፈጸመባትን፣ ሥርዓተ ጥምቀት ያካሄደባትን፣ ጸዋትወ መከራ የተቀበለባትን፣ ለሞት ተላልፎ የተሰጠባትን፣ ሞትን ድል አድርጎ በክብር የተነሣባትን፣ ያረገባትንና ብርሃነ መለኮቱን የገለፀባትን ፣ቅድስት አገር ኢየሩሳሌምን ይጎበኙ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪ ቀርቦልዎታል።

ዕድሉይድረስዎእስከመቼበምኞትብቻይወሰናሉ፣
በመጠነኛዋጋበተስማሚጊዜኢየሩሳሌምንይጎብኙ።

የትንሣኤ መርሐ ግብር ተካፋይ መሆን እንዲችሉ ፕሮግራሙ የሚከናወንበት ዕለት በ 11 ሌሊት አዳር በ 12 ቀን ቆይታ የሚጠቃለል ይሆናል።

የትንሣኤን በዐል በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም እንዲያሳልፉ ይህን ማስታወሻ ስናቀርብልዎ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት በተናጠልም ሆነ በህብረት ተደራጅተው መጎብኘት ለሚሹ ሁሉ የተመቻቸ እንዲሆን በማድረግ ነው።

ከሀገር ቤት ወላጆችዎን በማስጎብኘትና ቅዱሱን ሥፍራ በማሳለም ከእናት ከአባትዎ ምርቃት ቢያስፈልግዎ ሁሉንም የጉዞ መስመር፣ ቪዛና የአየር ትኬት የመሰለውን አስፈጽመን ኢየሩሳሌም ማዕከለ ምድር እንድትገናኙ እናደርጋለን።

በተጨማሪም በቅድሰት አገር ኢየሩሳሌም በደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት ገዳም በአባቶች ቡራኬ በሥርዓተ ተክሊል ቅዱስ ጋብቻ ለመፈጸም ለሚመኙ እና በቃና ዘገሊላ ቤተ መቅደስ ሥርዓተ ቀለበት ማድረግ ለሚጓጉ ፣በጎልጎታ ዴር ሥልጣን ገዳም ሥርዓተ ምንኩስና መቀበል ለሚሹ ሁሉ አስፈላጊውን ዝግጅት በማመቻቸት ተገቢውን አገልግሎት እንሰጣለን።

ፕሮግራሙን ለመካፈል ሲወስኑ ከዚህ በታች ባለው አድራሻችን ሲመዘገቡ ሙሉ ዝርዝር ፕሮግራሙንና ዋጋውን መቀበል ይችላሉ። ከየትኛውም ቦታ ሆነው በኢሜለ አድራሻ ወይም በስልክ ጠይቀው መረዳትና መመዝገብ ይችላሉ።

የፕሮግራማችን ተካፋይ ለመሆን በመወሰንዎ በቅድሚያ እናመሰግናለን ::

Ghion Travel Services

Address

1118 9th Street NW # 200 Washington DC 20001

Fax

202 588 1190

የኢትየጵያትንሣኤበዐል
በኢየሩሳሌምየቅዱሳትመካናትመንፈሳዊጉብኝትዝርዝርፕሮግራም

Day 1

የተደራጁት ምዕመናን እሥራኤልቤንጎርዮንአውሮፕላንማረፊያእንደደረሱበኢየሩሳሌም የፕሮግራሙአዘጋጅናየኤጀንሲውባልደረቦችአቀበቀበልያደርጉላቸዋል:: በተዘጋጀላቸውአውቶቡስበአንድነትሆነውወደኢየሩሳሌምይጓዙናየሆቴልቁልፍይቀበላሉ:: በተመደበውሰዓትራትተመግበውአዳርይሆናል::

Day 2 (ጸሎተሐሙስ)

(በደብረ ጽዮን)መንደርጌታችንኢየሱስክርስቶስየደቀመዛሙርቱንእግርአጥቦእራትአብልቶ:- ምሥጢረቁርባንየሠራበትንቦታ:- ለሐዋርያትመንፈስቅዱስየወረደበትንጽርሐጽዮንቤተክርስቲያን:- ቅድስትድንግልማርያምየተገነዘችበትንቅዱስሥፍራይሳለማሉ:: በመቀጠልየእሥራኤልቀደምትነገሥታትመቃብርመታሰቢያየሆነውንምኩራብሃይማኖታዊናታሪካዊቦታይጎበኛሉ::

Day 3 (ዓርብ ስቅለት)

በጧት ወደ ጌቴሴማኒ ይጓዛሉ ::- በጌቴሴማኒ ጌታችን የጸለየበትን “አፀደ ሐምል” የተባለውን የአትክልት ሥፍራ:- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተቀበረችበትን ና በክብር የተነሣችበትን ዋሻ (ቤተ መቅደስ) ይሳለማሉ :: በጉዞ ላይ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተወግሮ ሰማዕትነት የተቀበለበትን ቦታ ይጎበኛሉ::- ወደ አሮጌው ከተማ በእግር በመጓዝ ቅድስት ድንግል ማርያም ያደገችበትን “ቤተ ሐና ወ ኢያቄም” የተባለውን የዋሻ ቤተ መቅደስ ይጎበኛሉ :: ቀጥሎም የ 38 ዓመታት ህመምተኛው መፃጉዕ የተፈወሰበትን “ቤተ ሳይዳ” የተባለውን ሥፍራ ያያሉ :- ይሁዳ ጌታችንን ለማስያዝ የተቀበለውን ገንዘብ በቤተ መቅደስ መልሶ እራሱን የሰቀለበትን ቦታ በጉዞ ላይ ይመለከታሉ ::

ከዚያ የጲላጦስ አደባባይ አንደደረሱ የምዕራፍ አንድ ታሪክ የገለጽላቸዋል። ቀጥለውም ሊቶስጥራ ተብሎ ወደሚጠራው ዋሻ በመግባት በሁለታኛው ምዕራፍ የጸሎትና ምህላ ሥነ ሥርዓት ተደርጎ ክቡር መስቀሉን ተሸክሞ በፍኖተ መስቀሉ ጎዳና በሚደረገው መንፈሳዊ ጉዞ ተካፋይ በመሆን፣ በጌታችን ላይ የተፈጸመውን ጸዋትወ መከራ እያሰቡበየምዕራፋቱ በካህኑ መሪነት ቅዱስ ወንጌል እየተነበበ፣ የሰቆቃው ትምህርት እየተሰጠ፣ የዕለቱ መሪር የሐዘን ዝማሬ እየተዘመረ፣እስከ ዴር ሥልጣን ገዳም ድረስ ይጓዛሉ:: ከዚያ የበዓለ ስቅለቱን ግብረ ሕማማት በመስማት::- ስግደት በመስገድ ይውላሉ:: ጥብጣቤ ተደርጎ፣ንሴብሆ ተብሎ፣የእግረ መስቀሉ ጉዞ መርሐ ግብር ተፈጽሞ ስንብት ሲሰጥ ወደ ሆቴል በመመለስ እራት ተመግበው አዳር ይሆናል::

Day 4 ( ቀዳም ሥዑር)

ጧት ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ይጓዛሉ:: ደብረ ዘይት እንደሌሎቹ ቦታዎች ሁሉ የተቀደሰ ቦታ መሆኑን በቅዱሳት መጻሕፍት ተነግሮለታል ። በዚህ ተራራ ቦታ ዙሪያ ጌታችን የፈጸማቸውን እንመለከታለን።በቤተ ፋጌ የሆሣዕናው ጉዞ በተጀመረበት የውርንጭላዋ ግርግምባለበት የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርሰቲያን አውደ ምህረት ትምህርት ይሰጠል የጎበኛል:- ጌታችን በክብር ያረገበት“ዕርገት”የተባለው ቦታ;- ቀጥሎ ጌታችን አቡነዘበሰማያት ትምህርት ያስተማረበት እና ማታ ማታ ያድርበት ነበር የተባለው“የኤሌዎን” ዋሻ ይጎበኛል :: ከዚያ ወደ ሆቴል ተመልሰው ምሳ ይመገቡና ዕረፍት ያደርጋሉ ::

ለትንሣኤው በዓል አከባበር አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ወደ አሮጌው ከተማ ለመጓዝ ይንቀሳቀሳሉ:: ለበዓሉ ክብር መላው ምዕመናን በሀገር ልብስ አሸብርቀው ወደ መንበረ ሊቀ ጳጳሱ ግቢ ያመራሉ :: ከዚያ መስቀሉን አጅበው ዝማሬ እየዘመሩ ወደ ደብረ ሥልጣን ገዳም ይጓዛሉ::- በአውደ ምህረቱ ዘሪያ ብርሃን ተይዞ በሚደረገው ሥርዓተ ዑደት ላይ የጧፍ ብርሃን ይዘው እየዞሩ ያከብራሉ:: የሌሊቱን ቅዳሴ አስቀድሰው በረከት ይቀበላሉ :: የሌሊት መግደፊያ እራት በዚያው ከምዕመናኑ ጋር ተቋድሰው ወደ ሆቴል ይመለሳሉ::

Day 5 ( በዐለ ትንሣኤ)

ጧት ቁርስ ተመግበው እረፍት ያደርጋሉ:: ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ለትንሣኤው ክብር በተዘጋጀው ልዩ የፋሲካ ምሳ ፕሮግራም ላይ በመገኘት በዓሉን በሀገር ባህል ሥርዓት ያከብራሉ:: በምሳው ሰዓት ላይ የእርስ በእርስ ትውውቅ ይደረጋል።የበዓሉ ወግ በምሑራንና በተጋበዙ ዕውቅ እንግዶች ይቀርባል:: ምሽቱ ላይ ወደ ሆቴል በመመለስ እራት ተመግበው አዳር ይሆናል::

Day 6 (ማዕዶት)

ጧት በ 11 ሰዓት ወደ ደብረ ገነት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ቅዳሴ ያስቀድሳሉ :: ቁርሰ ተመግበው ክፍል ይለቁና ቁልፍ ያስረክባሉ :: ከዚያ ወደ ጥብርያዶስ ከተማ ጉዞ ይጀምራሉ :: በቅድሚያ በኢያሪኮ ከተማ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ጸሎት ተደርሶ በጸበሉ ለበረከት ይረጫሉ ::ቆሮንቶስ ገዳም በመውጣት ጌታችን 40 ቀን 40 ሌሊት የጸለየበትንዋሻ ቤተ መቅደስ ይሳለማሉ :: በመቀጠል በነቢዩ ኤልሳ ስም የሚጠራውን ምጭ ተመልከተው በካህኑ ተባርኮ በጸበልነቱ ይረጫሉ ይጠጣሉ :: በአካባቢው ምሳ ተመግበው በዘኪዎስ ስም የሚጠራውን ዋርካ ዛፍ :ቀጥሎ የኢትዮጵያን ገዳም ቤተ ገብርኤል ይሳለማሉ ይጎበኛሉ :: በመቀጠል ወደ ጥብርያዶስ በማምራት “Ron beach” በተባለው ሆቴል የክፍል ቁልፍ ተረክበው እራት ይመገቡና አዳር ይሆናል::

Day 7

ቁርስ ተመግበው ወደ ቅፍርናሆም ጉዞ ያደርጋሉ :: በቅድሚያ በዮርዳኖስ ወንዝ መውረጃ ጫፍ ላይ በተዘጋጀው መጠመቂያ ሥፍራ ጸሎተ ወንጌል ተደርሶ ፣ውሃው በካህናቱ ተባርኮ በረከት ለማግኘት በሥነ ሥርዓት ገብተው ይነከራሉ :: በመቀጠል ወደ ቅፍርናሆም መንደር በመጓዝ ጌታችን አንቀጸ ብፁዓንየተባለውን ትምህርት ለሕዝቡ ያስተማረበትን ተራራማ ቦታና ቤተ መቅደስ፣(የሐዋርያው ማቴዎስ ቤት)ቅዱስ ማቴዎስን ከቀራጭነት ለሐዋርያነት የመረጠበት ቅዱስ ሥፍራ እና ጌታችን ሁለት አሣና አምስት ህብስት ባርኮና አበርክቶ የመገበበትን የበረከት ሥፍራ እንዲሁም ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ በዳግም ትንሣኤ ለሦስተኛ ጊዜ የተገለጠበትን፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ካህን ሆኖ የተሾመበተን ቤተ ክርስቲያን ይጎበኛሉ :: በመቀጠልም “ኮራዚንና ቤተሳይዳ”የተባሉትን የጠፉ ከተሞች በሩቅ እየተመለከቱ ቅፍርናሁም መንደር ይደርሳሉ። ከዚያ ጌታችን ያስተማረበትንና ታላላቅ ገቢረ ተአምራት ያከናወነበት ከተማ፣ የከተማዋ ፍርሰራሽ ጥንታዊውን የአይሁድ ምኩራብ ታሪካዊ ቦታ እየተዘዋወሩ ይመለከታሉ::ይህ ብዙዎቹ ሐዋርያት ለሐዋርያነት ተልዕኮ የተመረጡበት የባህር ዳርቻ ነው።ብዙ ህመምተኞች በጌታችን እጅ ፈውስ ያገኘበት መንደር ነው።በባሕሩ ዳርቻ ምሳ ይመገባሉ :: ከዚያ በመርከብ ላይ ተሳፍረው በባሕሩ ላይ የተፈጸመው ትምህርት እየተሰጠ፣ ዝማሬ እየተዘመረ ጉዞ ይደረጋል :: በመጨረሻ ወደ ሆቴል ተመልሰው እራት ይመገቡና አዳር ይሆናል::

Day 8

ጧት ቁርስ ይመገቡና ወደ ናዘሬት ከተማ ጉዞ ያደርጋሉ :: በቅድሚያ በደብረ ታቦር ተራራ ብርሃነ መለኮቱ የተገለጠበትን ሥፍራ:- በቃና ዘገሊላ መንደር ጌታችን በሠርጉ ቤት ተገኝቶ ውሃን ወደ ወይን በመለወጥ የመጀመሪያውን ተአምራት የፈጸመበትን ሥፍራ ተሳልመው ይጎብኛሉ:- በአካባቢው ምሳ ይመገባሉ :: በመቀጠልም

በናዝሬት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብሥራት የተቀበለችበትን እና ቤተ ዮሴፍ የተባለውን ሥፍራ እንዲሆም እመቤታችን ውሃ ትቀዳበት የነበረውን ምንጭ ቦታና በላዩ ላይ የታነፀውን ቤተ ክርስቲያን እየተዘዋወሩ ጎብኝተው ከዚያ ወደ ሆቴል በመመለስ እራት ተመግበው አዳር ይሆናል::

Day 9

ጧት ቁርስ ቁርሰ ተመግበው ክፍል ይለቁና ቁልፍ ያስረክባሉ :: ወደ ቴል አቪብ ከተማ ጉዞ ለማድረግ ይንቀሳቀሳሉ ::ሐይፋ ከተማ እንደደረሱ በቀርሜሎስ ተራራ ነቢዩ ኤልያስ ጣዖታቱን ድል ያደረገበት ቤተ ክርስቲያን ይጎበኛል :: የሐይፋን የባሕር ወደብ በርቀት በማጉሊያ መነፅር ይመለከታሉ :: በአካባቢው ምሳ ከተመገቡ በኋላ የሜዲትራንያንን ባህር እያማተሩ፣ የአካባቢውን ልምላሜ እያደነቁ፣የቴል አቪቭን ከተማ አቋርጠው በያፎ (ጅፋ)ከተማ ጥንታዊውን የባህር ወደብ ጎብኝተው በአሮጌው መንደር ውስጥ የቅዱስ ጴጥሮስን “ጣቢታ ቁሚ” የተባለበተን ቤተ መቅደስ ይጎበኛሉ ::(ይህ የባሕር ወደብ በመጽሐፍ ቅዱስ ኢዮጴ ተብሎ የሚጠራው ነው።ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ባሠራ ጊዜ ከሊባኖስ ተጭኖ የመጣው ዝግባ የተራገፈው በዚህ ወደብ ሲሆን ፣ነቢዩ ዮናስም በመርከብ ተሣፍሮ ወደ ተርሴስ ለመሄደ የተነሣው ከዚህ ሥፍራ ነበር።) እንዲሁም ሉድ ወደ ተባለው ከተማ በማምራት የሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ጎብኝተው ወደኢየሩሳሌምይጓዙናበ Dan ሆቴልቁልፍይቀበላሉ:: እራት ተመግበው አዳር ይሆናል::

Day 10

ጧት ቁርስ ይመገቡና ወደ ቤተ ልሔም ያመራሉ :: በቤተ ልሔም ጌታችን የተወለደበትን ዋሻ ቤተ መቅደሱንና የወተቱ ዋሻ የተበለውን ቤተ መቅደስ እንዲሁም መካነ ሰላም ኢየሱስ የኢትዮጵያን ገዳም በቅደም ተከተል ይጎበኛሉ::

ምሳ በኣባቢው ተመግበው ወደ ሄብሮን ከተማ ያመራሉ :: በሄብሮን “የአበው መቃብር” የአብርሃምና ቤተ ሰቦቹ መቃብር የተባለውን በጥንቱ ቤተ ክርስቲያን አሁን ቤተ ምኩራብ እና ቤተ መስግድ የሆነውን ታላቅ ሥፍራ ይጎበኛሉ :: ደገኛው አብራሃም ሥላሴን ተቀብሎ ያስተናገደበትን ሥፍራ “አጸደ መምሬ” ይጎበኛሉ :: ከዚያ ወደ ሆቴል በመመለስ እራት ተመግበው አዳር ይሆናል::

Day 11

ጧት ቁርስ ይመገቡና ወደ ኢያሪኮ ከተማ ይጓዛሉ :: በቅድሚያ በቢታንያ መንደር የአልአዛርን ቤተ ክርስቲያንአልአዛር የተቀበረበትን ዋሻ እንዲሁም የተክለ ሃይማኖትን ገዳምና ቤተ አረጋውያኑን ይጎበኛሉ :: ምሳ በገዳመ ቆሮንቶሰ አካባቢ ይመገባሉ :: በመቀጠል ወደ ሎጥ በህር በማምራት በዚያ ቆይታ ያደርጋሉ :: በጨዉ ውሃ መታጠብ መነከር የሚሹ ሁሉ ቅድም ዘግጅት አድርገው መምጣት እንዳለባቸው ይነገራል :: ምሽቱ ላይ ወደ ሆቴል በመመለስ እራት ተመግበው አዳር ሆናል::

Day 12

የዳግም ተንሣኤን በዐል በዴር ሡልጣን ገዳም በማስቀደስ ያከብራሉ :: ቁርስ በአካባቢው ተመግበው ወደ ዓይነ ከርም መንደር ይጓዛሉ:: በዚያ የዘካርያስንና የኤልሳቤጥን እንዲሁም የቅዱስ ዮሐንስን ቤተ መቅደሶች:- እንዲሁም እመቤታችን ከኤልሳቤጥ ጋር የተገናኘችበትን ቅዱስ ሥፍራ ይሳለማሉ ::በመቀጠል ያድ ባሼም (YAD VASHEN)ወይም ሆሎኮስት (Holocaust)ተብሎ ወደ ሚጠራው በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ላለቁት የ 6 ሚልዮን አይሁዳውያንን ታሪክ የያዘውን መካነ መዘክር እየተዘዋወሩ ይጎበኛሉ።

ምሳ በአካባቢው ተመግበው ወደ አሮጌው ከተማ ገብተው እቃ እንዲገዛዙ ጊዜ ይሰጣል:: ምሽቱ ላይ ወደ ሆቴል ተመልሰው እራት ይመገባሉ:: በዚህን ጊዜ መንገደኞቹ ሁሉ እንደተለመደው በአንደነት ተሰባስበው የመሰነባበቻ ጸሎት ያደርሳሉ:: ምስጋናና የሐሳብ ለሐሳብ ልውውጥ ተደርጎ አዳር ይሆናል::

Day 13

ቁርስ ይመገቡና የሆቴል ክፍል በመልቀቅ ሻንጣዎቻቸውን አውርደው ቁልፍ ያስረክባሉ ::
መንገደኞች በመጡበት መስመር እንደ በረራ ሰዓታቸው ወደ አየር መንገድ ይጓዛሉ::- የፕሮግራሙ መሪና አስተናጋጁ አጅቦ በመሸኘት ፕሮግራሙ ይጠቃለልና የመጨረሻ ስንብት ይሆናል:: ፍጻሜውን እግዚአብሔር ያሳምረው::

ማሳሰቢያ:- በፕሮግራማችን መሠረት የረጅም ዓመታት ልምድና እውቀት በላቸው መሪዎች (ጋይዶች) አማካኝነት በየጉብኝቱ ሥፍራዎች ሁሉ ታሪካዊ ይዘቱ ገለጻ ይደረጋል:: መንፈሳዊ ትምህርቱ በምሑራን ይሰጣል:: ከሁሉም በላይ ልዩ ትኩረትና እንክብካቤ በማድረግ መንገደኞቻችንን ለማስደሰት ጥረት እናደረጋለን :: እግዚአብሔር ጉዞአችንን ይባርክልን::
አሜን……………